
ጎንደር: ጥር 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ከወላጆች፣ ከትምህርት ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና የሥራ ኀላፊዎች ጋር በሦስት የትምህርት ጉዳዮች ውይይት እያደረገ ነው።
መምሪያው በጸጥታ ችግር የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ማስጀመር እንደሚያስፈልግ የመከረ ሲኾን በከተማው ሰባት ትምህርት ቤቶች በጸጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ማቋረጣቸውን ገልጸዋል።
ትምህርት ቤቶቹ ወደ ሥራ እንዲገቡ እና ተማሪዎች እንዲማሩ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም የከተማ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ስንታየሁ ነጋሽ አሳስበዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ክልላዊ እና ብሔራዊ ፈተና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መምሪያው እየሠራ መኾኑን ኀላፊው ጠቅሰዋል። ማኅበረሰቡም ለተማሪዎች ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ-: አገኘው አበባው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!