
ሰቆጣ: ጥር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 29ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ በጉባዔው የ28ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤን፣ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት የአሥፈጻሚውን ዕቅድ ክንውን ሪፖርት፣ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት ኦዲት እና የሥርዓተ ጾታ ሪፖርት፣ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን የአፈጻጸም ሪፖርት እና የሚቀርቡ ሹመቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
ጉባኤው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይቆያል ተብሏል።
ዘጋቢ: ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን