የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የመንገድ ሴክተር ጉባኤ በጎንደር ከተማ እያካሄደ ነው።

65

ጎንደር: ጥር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ ሀገር አቀፍ የመንገድ ጉባኤው እየተካሄደ ነው።

በጉባዔው የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘወ ጨምሮ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የሥራ ኀላፊዎች እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በጉባኤው እንደ ሀገር ባለፉት ስድስት ወራት የነበረው የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው።

ዘጋቢ:- ደስታ ካሳ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በቅንጅት የሠሩ ተቋማት ጥሩ ፈጽመዋል” የሴቶች፣ ሕጻናት፣ ወጣቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ።
Next articleየአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር መድረክ እያካሄዱ ነው።