ተቋማትን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ለማድረግ እየተሠራ ነው።

25

ባሕር ዳር: ጥር 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ሕጻናት፣ ወጣቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሥሩ የሚቆጣጠራቸውን የትምህርት የጤና፣ የወጣቶች እና ስፖርት፣ የሴቶች ፣ ሕጻናት እና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮዎችን እንዲኹም የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎትን የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አድምጧል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ሀሳብ እና አስተያየት እየሰጡ ነው። ከአማራ ክልል አካል ጉዳተኞች ማኀበራት ፌዴሬሽን የተወከሉት መምህር ንጉሴ ምህረቱ እንዳሉት መስማት የተሳናቸውን ወገኖች ሀሳብ፣ ችግራቸውን እና ሕመማቸውን በአግባቡ ተረድቶ የሚያስተረጉምላቸው የጤና ባለሙያ ባለመኖሩ ችግራቸው የተደራረበ ኾኗል።

ሌላው አስተያዬት ሰጪ የብሬል መጻሕፍት ባለመኖሩ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል ትምህርታቸውን በመከታተል ተወዳዳሪ ለመኾን መቸገራቸውን ተናግረዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ እየሩስ መንግሥቱ ክልሉ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የብሬል መጻሕፍትን አሳትሞ ሥራ ላይ አውሏል ብለዋል።

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚኾኑ መጻሕፍትን የሚያሳትመው ትምህርት ሚኒስቴር መኾኑንም ጠቁመዋል። “ጥያቄውን እኛም የምንጋራው ስለኾነ እስቀድመን ለሚመለከተው አካል አድርሰናል” ነው ያሉት። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ እንዳሉት መስማት ለተሳናቸው ወገኖች የሚያስተረጉሙ የጤና ባለሙያዎች ሠልጥነዋል።

በ27 ሆስፒታሎች ውስጥ ሥራው ተጀምሯል ነው ያሉት። ቢሮ ኃላፊው ይህን በጎ ጅምር ለማስፋት እና ለማጠናከር ይሠራል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሕግ የበላይነትን ለማስከበር ቁርጠኛ መኾናቸውን የአድማ መከላከል እና መደበኛ ምልምል ሠልጣኞች ተናገሩ፡፡
Next articleበአማራ ክልል ያለው ግጭት ከቀጠለ በርካታ ወገኖች ለአዕምሮ ጤና ችግር ይጋለጣሉ ተባለ።