
ባሕር ዳር: ጥር 29/2017 ዓ.ም(አሚኮ) በብር ሸለቆ የመሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ሥልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ የ33ኛ ዙር የአድማ መከላከል እና መደበኛ ፖሊሰ ሠልጣኞች የሥልጠና እንቅስቃሴን በተመለከተ ግምገማ ተካሂዷል።
በጥሩ ወታደራዊ ሥነ ምግባር የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በስኬት ማጠናቀቅ በሚቻልበት ቁመና ላይ ስለመኾናቸውም ተነግሯል፡፡
የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የሥልጠናው አሥተባባሪ ኮማንደር አብዮት ሽፈራው እየተሠጠ የሚገኘው ሥልጠና የክልሉን ሕግ እና ሥርዓት በማሰከበር የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሂደት ውሰጥ ትልቅ ኀላፊነት የሚጠበቅባቸው እንደኾነ ተነግሯል።
በፖሊሳዊ ዕውቀት፣ በአመለካከት እና ሙያዊ ሥነ-ምግባር ማብቃት ላይ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በቁርጠኝነት እና በቅንጅት እየተሠራ መኮኑን አሥተባባሪው ገልጸዋል። የተሻለ የፖሊሰ ሠራዊት ለመገንባት ከዚህ የበለጠ ትጋት እንደሚጠበቅም ከአማራ ፓሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!