አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ጥፋተኞች መሆናቸው ተገለጸ፡፡

446

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 26/2012 ዓ.ም (አብመድ) ተከሳሾች አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ታደሰ ካሳ እና አቶ ዳንኤል ግዛው ላይ የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት ሥራን በማያመች መንገድ መምራት የሙስና ወንጀል በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ክርክር ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ፍርድ ቤቱ የከሳሽንና የተከሳሾችን ክርክር ሲያዳምጥ ከቆየ በኋላ ዛሬ ሚያዝያ 26/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት መዝገቡን መርምሮ 1ኛና 2ኛ ተከሳሾችን (አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳን) የጥፋተኝነት ብይን በመስጠት እና 3ኛ ተከሳሽን ከቀረበበት የወንጀል ድርጊት ነፃ ብሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ በ1ኛና 2ኛ ተከሳሾች ላይ ጥፋተኛ በተባሉበት ዐቃቤ ሕግና ተከሳሾች የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርቡ ለሚያዚያ 28/2012 ዓ.ም ቀጠሮ በመያዝ የዕለቱን ችሎት ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡

Previous articleአርሶ አደሮች በመስኖ በማልማት እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እያገኙ ነው፡፡
Next articleየደምበጫ ከተማ ነዋሪዎች ደም እየለገሱ ነው፡፡