
ባሕር ዳር: ጥር 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ሊካተቱ ይገባሉ ያላቸውን አጀንዳዎች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክቧል፡፡
የመገናኛ ብዙኀን ምክር ቤቱ ለኮሚሽኑ ዓላማ መሳካት ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መኾኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ ተናግረዋል፡፡
ምክር ቤቱ ማኅበረሰቡ ስለ ኮሚሽኑ ተግባራት መረጃ እንዲያገኝ በማድረግ የላቀ አስተዋጽ እያበረከተ መኾኑንም አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት ሰብሳቢ አማረ አረጋዊ በበኩላቸው ምክር ቤቱ ከሀገራዊ ምክክሩ ጋር የሚተሳሰሩ ጉዳዮችን ወደ ሕዝብ ለማድረስ በትኩረት መሥራቱን እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡
በአጀንዳ ርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ የመገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ አባላት እና ጋዜጠኞች መገኘታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!