ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ አተኩረው እንዲሠሩ ተጠየቀ።

39

ፍኖተ ሰላም: ጥር 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን ወጣቶች ሊግ ”ሀብት አፈራለሁ፤ የሀገሬን ሰላም እጠብቃለሁ፤ የኢትዮጵያን ብልፅግና አፋጥናለሁ!” በሚል መሪ መልዕክት ከወጣቶች ጋር የሰላም እና ልማት የንቅናቄ መድረክ በፍኖተ ሰላም ከተማ እያካሄደ ነው።

በድረኩ የተገኙት በምዕራብ ጎጃም ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ሙላት ጌታቸው ለአንድ ሀገር እድገት መፋጠን የወጣቶች ሚና የጎላ መኾኑን ገልጸዋል። ወጣቶች በልማት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ሁሉ በሰላም ግንባታ ላይም አተኩረው መሥራት እንዳለባቸውም ነው ያሳሰቡት።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ወጣቶች ሊግ ኀላፊ በላቸው ፈጠነ የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት የሚረጋገጠው የሀገሪቱን ሀብት በተገቢው መንገድ መጠቀም ሲቻል ብቻ ነው ብለዋል። በመኾኑም ሀብት ሊፈራ የሚችለው ሰላምን ቀድሞ ማረጋገጥ ሲቻል ብቻ በመኸኑ ወጣቶች የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

በመድረኩ ሰነድ ቀርቦ ከተለያዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው። በውይይት መድረኩ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መሪዎች፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን የሥራ ኀላፊዎች እና ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ወጣቶች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰውን ተክቶ የሚሠራው አዲስ ቴክኖሎጂ!
Next articleከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ ወስደዋል።