
ባሕር ዳር: ጥር 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ምክር ቤት የንግድ፣ ኢንዱሥትሪ እና ከተማ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን የመንግሥት ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው። ቋሚ ኮሚቴው በሁለተኛ ቀን የሥራ ግምገማው በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ አስተያየት እና ጥያቄዎችን እየተቀበለ ነው።
ቋሚ ኮሚቴው በሥሩ ተጠሪ የኾኑትን የማዕድን ሃብት ልማት፣ የከተማ እና መሠረተ ልማት፣ የመንገድ፣ የንግድ እና ገበያ ልማት፣ የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት፣ የሥራ እና ሥልጠና ቢሮዎች እንዲሁም የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ባለሥልጣንን ሪፖርትን በውይይቱ መጀመሪያ ቀን ማዳመጡ ይታወሳል።
ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!