
ጎንደር: ጥር 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ ሚኒስቴር ድኤታዎች፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የሥራ ኀላፊዎች ናቸው ጎንደር ከተማ የገቡት።
በቆይታቸውም በጎንደር ከተማ በመልማት ላይ የሚገኙ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ምልከታ የሚያደርጉ ሲኾን በከተማ የልማት ተግባራት ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!