የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የደረጃ ማሻሻያ ግንባታ በጥራት እና በፍጥነት እየተከናወነ ነው።

62

ባሕር ዳር: ጥር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ሕጻናት፣ ወጣቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው። የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ እና የፊፋን መሥፈርት ባሟላ መልኩ በመገንባት አፈጻጸሙ 83 በመቶ መድረሱን የክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ እርዚቅ ኢሳ ተናግረዋል።

የቢሮው ኀላፊው በክልሉ 25 ሀገር አቀፍ መሥፈርትን ያሟሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ተለይተዋል ብለዋል። ከ300 በላይ የጥርጊያ ሜዳዎች ተስፋፍተዋል ያሉት አቶ እርዚቅ በትምህርት ቤቶች እና ተቋማት ደግሞ 240 የማዘውተሪያ ሥፍራዎች ተለይተው ወደ ተጨባጭ ተግባር ገብተዋል ብለዋል።

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም በገቢ ራሱን ለማስቻል እንዲችል የአገልግሎት ክፍሎች ሥራ መጀመራቸውን ቢሮ ኀላፊው ጨምረው አብራርተዋል። የስታዲዬሙ የደረጃ ማሻሻያ ግንባታ በጥራት በፍጥነት እየተከናወነ ነው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ማኝናውንም ዓይነት ድሮን ያለ ብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ፈቃድ ማስነሳትም ኾነ ማብረር እንደማይቻል ተገለጸ፡፡
Next articleበአካባቢው የሚገኙ የማዕድን ጸጋዎችን ለይቶ ለመጠቀም እየተሠራ መኾኑን የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር አስታወቀ።