
ባሕር ዳር: ጥር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ሕጻናት፣ ወጣቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጤና ቢሮን የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም በባሕር ዳር ከተማ እየገመገመ ነው።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ ባለፉት ስድስት ወራት ከ226 ሺህ በላይ የሚኾኑ እናቶች በጤና ተቋማት መውለዳቸውን ተናግረዋል።
ቢሮ ኀላፊው የማሕጸን በር ካንሰር የመከላከያ ክትባት በስፋት መሰጠቱን ገልጸዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ ሰፊ የወባ በሽታ ስርጭት ነበር ያሉት ቢሮ ኀላፊው ከ1ሚሊዮን በላይ ሰዎች የወባ በሽታ ተገኝቶባቸዋል።
ከዚህ ውስጥ ከ152 ሺህ በላይ ከአምስት ዓመት በታች ናቸው።
ማኀበረሰቡ ኤች አይቪን በመከላከሉ ረገድ መዘናጋት እየታየበት በመኾኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተጠቁሟል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን