
ባሕር ዳር: ጥር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ጀስቲስ ፎር ኦል በትብብር በመሥራት የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርአቱ ውጤታማነትን ማደበር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
በተለያዩ ደረጃዎች የሚደረጉ የሰው ሀብት አቅም ግንባታ ሥራዎች ፣ የጉዳዮች ፍሰት አሥተዳደር ፣ የሕግ ጥናት ፣ ምርምር እና ረቂቅ ዝግጅት ፣ አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ማጠናከር ፣ የዳኞች እና የፍትሕ አካላት ትብብር ላይ የሚተገበሩ ሥራዎች ፣ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ፣ መዝገቦችን ማጥራት ፣ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ማሳደግ እና የፍትሕ ሥርአቱን ተዓማኒነት ማጠናከር ላይ በጋራ ለመሥራት ነው ስምምነት የፈጸሙት።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው እና የጀስቲስ ፎር ኦል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፓስተር ዳንኤል ገብረሥላሴ ናቸው፡፡
ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ስምምነቱ የፍርድ ቤቱን የሰው ኃይል እና አገልግሎት አሰጣጥን በማጠናከር የፍትሕ አሥተዳደር ሥርዓት ግንባታ ላይ ትልቅ ውጤት እንደሚያመጣ ተገልጿል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!