ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ የመማሪያ መጻሕፍት ተሰራጭቷል።

34

ባሕር ዳር: ጥር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ሕጻናት፣ ወጣቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ቢሮን የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም በባሕር ዳር ከተማ እየገመገመ ነው። በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እንዳሉት በክልሉ የሚገኙ አብዛኞቹ ነባር ትምህርት ቤቶች ደረጃቸው አነስተኛ ነው።

በአዲስ እየተገነቡ ያሉ ትምህርት ቤቶች ግን ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲኾኑ ተደርጓል ነው ያሉት። ዶክተር ሙሉነሽ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ4 ሚሊዮን በላይ የመማሪያ መጻሕፍት ተሰራጭቷል ብለዋል።

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደግሞ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን መጻሕፍት በማሳተም ከ5 ሚሊዮን በላይ የመማሪያ መጻሕፍት ለትምህርት ቤቶች መሰራጨቱን ነው የተናገሩት።

በሰሜኑ የጦርነት ወቅት ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሚኾኑ ተማሪዎች ለሥነ ልቦና ጉዳት መዳረጋቸውን ያስታወሱት ዶክተር ሙሉነሽ አሁን ክልሉ በገጠመው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ወጭ ኾነዋል። በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ መኾናቸውንም በመጠቆም።

ከትምህርት ገበታ ውጭ የኾኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ሁሉም በርብርብ መሥራት እንዳለበት ዶክተር ሙሉነሽ ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የንግዱ ዘርፍ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል” የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ
Next articleየአራት ኪሎ ፕላዛ የእግረኞች የውስጥ ለውስጥ ማሳለጫ መንገድ ግንባታ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።