
አዲስ አበባ: ጥር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “የግሉ ዘርፍ ሚና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ግንባታ” በሚል መሪ መልዕክት የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስቴር እና ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተር ፕራይዝ ከተባለ የአሜሪካ ተቋም ጋር በመኾን የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሠብሥብ አባፈራ ሰላም የንግድ የደም ሰር ነው ብለዋል። ምርት እንዲቀንስ፤ ዜጎች ባልተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖሩ፤ ምርት እና ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ እንዳይኖሩ፤ ኢኮኖሚያዊ ሁነት በአግባቡ እንዳይከውን ያደርጋል ነው ያሉት። በዚህም የግሉ ዘርፍ በሀገሪቱ ሰላም እንዲመጣ ሚናው የላቀ ሊኾን ይገባል ብለዋል።
የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እድሪስ ማኅበረሰባዊ ትስስር እንዲጠናከር እና ከሌሎች ሀገሮች ጋር ያለው መስተጋብር እንዲጠናከር ያደረገው ንግድ ነው ብለዋል።
ንግድ ሰላምን ለመመለስ ለሚደረገው ሥራ ትልቅ መሳሪያ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ዘርፉ በቅድመ ግጭት እና ድኅረ ግጭት ወቅት ሚናውን በመወጣት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!