
ባሕር ዳር: ጥር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት የበጀት ምንጭ የተገነባው የአልፋ ምድር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቅቆ ለአገልግት ክፍት ኮኗል።
ትምህርት ቤቱ 10 መማሪያ ክፍሎች አሉት ተብሏል። ደረጃውን የጠበቀ መፀዳጃ ቤት፣ የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ፣ ሻወር እና ሌሎች ለትምህርት ጥራት መሻሻል አስፈላጊ የኾኑ ደረጃዎችን በማካተት በጥራት የተሠራ እንደኾ ተመላክቷል።
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ጣልባቸው በቀለ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ያሉ ችግሮችን በመቋቋም ግንባታውን ላጠናቀቀው ተቋራጭ፣ በጀት ለፈቀደው ትምህርት ሚኒስቴር፣ ሥራውን በመከታተልና በመደገፍ አስተዋፅዖ ለነበራቸው ባለሙያዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የአልፋ ምድር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ዘነበ መግቢያነህ በተሠራው ሥራ ደስተኛ መኾናቸውን ገልጸዋል። ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት እንደሚያስችልም አንስተዋል። ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው
ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!