
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቡርኪና ፋሶ ወደ ፍራንክፈርት ከ22 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የጭነት በረራ ማድረጉን አስታወቀ።
አየር መንገዱ 52 ቶን የሚመዝን የፍራፍሬ ምርት እንዳጓጓዘ ተገልጧል፡፡
በቀጣይም አገልግሎቱን ይበልጥ በማስፋት ዘወትር ከአፍሪካውያን ጎን እንደሚቆም አስታውቋል።
አየር መንገዱ በቅርቡ ለጭነት አገልግሎት እንዲውሉ ከተስተካከሉ የመንገደኞች አውሮፕላኖች መካከል የቦይንግ B-777 አውሮፕላንን ለዚህ አገልግሎት መጠቀሙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡