
አዲስ አበባ: ጥር 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ከሚኒስትር ዴኤታዎቻቸው ጋር በመኾን አሚኮ በአዲስ አበባ ገንብቶ ያስመረቀውን ዘመናዊ ስቲዲዮ ጎብኝተዋል።
አሚኮ ለዚህ በመብቃቱ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። አሚኮ በ12 ቋንቋዎች በመሥራት አብሮነትን በማጠናከር የአማራን ሕዝብ ብቻ ሳይኾን ሁሉንም ኢትዮጵያውያ እያገለገለ ስለመኾኑ ተናግረዋል።
አሚኮ በአዲስ አበባ ያስመረቀው ስቱዲዮ ተቋሙ በየጊዜው የሚሻሻል ትልቅ ተቋም ለመኾኑ ማሳያ ነው ብለዋል ሚኒስትሯ።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የዜጎች ሰላም፣ ልማት እና ትስስር እንዲጠናከር የተጋ ሚዲያ ነው ያሉት ሚኒስትሯ የትውልድ ግንባታ ሚናው ትልቅ መኾኑንም ጠቅሰዋል።
አሚኮ በጋራ ሀገር ግንባታ ትርክት ሚናው ትልቅ ነው፤ ከዚህም በላይ የዜጎችን መስተጋብር ለማጠናከር እና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለመፍጠር ጠንክሮ ሊሠራ ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ሙሉቀን ሰጥየ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን በአሚኮ ስቱዲዮ ግንባታ ወቅት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የምስጋና እና እውቅና ሰርተፊኬት ሰጥተዋል።
አሚኮ አዲስ አበባ ላይ ያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን በእውነተኛ እና ተአማኒ መረጃ ተደራሽነት ለማገልገል ተጨማሪ ግብዓት እንደሚኾንም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!