“የእንስሳት በሽታን ተጽዕኖ በመረዳት ችግሩን በጋራ ትብብር ልንሻገረው ይገባል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

39

ባሕር ዳር: ጥር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ 26ኛውን የዓለም እንስሳት ጤና ድርጅት የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤ አስጀምረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የእንስሳት በሽታ በእንስሳት ተዋፅዖ ውጤቶች ምርታማነት እና በዜጎች ጤናማ አኗኗር ላይ ያለውን ቀጥተኛ ተጽዕኖ በመረዳት ችግሩን በጋራ ትብብር ልንሻገረው ይገባል ብለዋል።

ዛሬ 26ኛውን የዓለም እንስሳት ጤና ድርጅት የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤ አስጀምረናል ነው ያሉት።

በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር፣ በመኖ አቅርቦትና ጥራትን ለማሻሻል በሠራነው ሥራ በንጥረ ነገረ የበለፀገ ምግብ በማምረት የአመጋገብ ስርዓታችንን ለማሻሻል እና የእንስሳት ጤና እንዲጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

እንደ አህጉር የሚፈትነንን የእንስሳት በሽታ ለመከላከልም ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩትን ከማቋቋም አንስቶ ድንበር ዘለል የእንስሳት በሽታዎችን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውነናል ነው ያሉት።

የእንስሳት ሕክምና አገልግሎት እንዲጠናከር በእንስሳት እና በእንስሳት ተዋጽኦ ንግድ ዘርፍ ያሉ የጤና አጠባበቅ ሕግጋት መከበር ላይ እንደዚህ ያሉ ጉባኤዎች ከፍተኛ ሚና ስለሚኖራቸው ይህ ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባለፉት ስድስት ወራት 27 ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት መኾናቸውን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር አስታወቀ።
Next article“8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሟል “ግብርና ቢሮ