የሕዝብን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል ወታደራዊ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸውን የፍኖተ ሰላም ተመራቂ ሚሊሻዎች ተናገሩ።

31

ባሕር ዳር: ጥር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በፍኖተ ሰላም ማዕከል ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የፍኖተ ሰላም ቀጣና የ2ኛ ዙር የሰላም አስከባሪ እና የሚሊሻ አባላት የምረቃ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

ተመራቂዎቹ የአካባቢያቸውን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል አካላዊ እና ወታደራዊ ሥልጠናዎችን በሚገባ ስለመውሰዳቸው በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ሠራዊት የሰላም ማስከበር ማዕከል ኀላፊ ሜጀር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴን ጨምሮ የዞን እና የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር መሪዎች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዝቡ በፍትሕ ተቋማት ላይ አመኔታ እንዲፈጥር የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት በትብብር ሊሠሩ እንደሚገባ ተጠቆመ።
Next article“ጉባኤው ዓላማውን ባሳካ መልኩ ተጠናቅቋል” አቶ አደም ፋራህ