ባለፉት ስድስት ወራት ከ58 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከንክኪ ነጻ መደረጉን የአማራ ክልል አካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።

26

ባሕር ዳር፡ ጥር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የግብርና፣ አካባቢ ጥበቃ እና የውኃ ሃብት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው። የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር በልስቲ ፈጠነ የአጣና ምርትን ከቦታ ቦታ ለሚያዘዋውሩ ግለሰቦች ፍቃድ በመስጠት ሃብቱ በሕጋዊ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል ነው ያሉት።

ባለፉት ስድስት ወራት ከ58 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ከንክኪ ነጻ በማድረግ አካባቢው መልሶ እንዲያገግም እና ብዝኀ ሕይዎቱ መልሶ እንዲያንሰራራ መደረጉ በሪፖርቱ ቀርቧል። በየአካባቢው የሚቋቋሙት ፕሮጀክቶች በአካባቢው ላይ ተጽዕኖ አለማሳደራቸውን እየተገመገሙ ነው ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ የሕግ ጥሰት በፈጸሙ 57 ፕሮጀክቶች ላይም አሥተዳደራዊ እና ሕጋዊ ርምጃ ተወስዷል።

ከኀብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ከፍተኛ የድምጽ ብክለት እየፈጠሩ የማኀበረሰቡን የቀን ከቀን ሕይዎት በሚያውኩ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይም እርምት ተሰጥቷል። የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድን በተመለከተ ክትትል እና ድጋፍ መደረጉን ምክትል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በአካባቢ እና ደን ጥበቃ ዘርፍ ለተሰማሩ ከ55 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯልም ተብሏል። ባለፉት ስድስት ወራት ባለሥልጣኑ ከደን ውጤቶች 57 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተጠቁሟል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተፈናቃዮችን መደገፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ።
Next articleበብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተመረጡ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፦