ሀገራዊ አጀንዳ ምን አይነት ቅርጽ ሊኖረው ይችላል?

35

ባሕር ዳር: ጥር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ የፓለቲካ እና የሀሳብ መሪዎች፣ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሠረታዊ በኾኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች መኖራቸው ተጠቅሶ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መመሥረት እንደምክንያት ተቀምጧል፡፡

👉እጅግ መሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ሊባሉ የሚችሉ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? የሚለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ይህንን ጉዳይ ለመረዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ መገንዘብና መሬት ላይ ያሉ እውነታዎችን ማየት ይጠይቃል ብሏል።

በእርግጥ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ያለፉ ሀገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየን የአጀንዳ አይነቶችን በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ መገደብና መወሰን ሂደቱን ለትችት ከመዳረጉም በላይ ተዓማኒነቱን ሊያሳጣው እንደሚችል ዕሙን ነው ይላል ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ።

ኮሚሽኑ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ያሻል ብለው ያመኑባቸውን የአጀንዳ ሀሳቦች በሕዝባዊ ውይይቶች እንዲያነሱ ሲያበረታታ መቆየቱን አስታውቋል።

ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችሉ ወሳኝና እጅግ መሠረታዊ የኾኑ ሀገራዊ ጉዳዮቻችንን ወደ ጠረጴዛ አምጥቶ ምክክር ማድረግ ትርፋማ ያደርገናል ይላል።

መግባባት የሚጠይቁን ‘’እጅግ መሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች’’ ምን ዓይነት ዋና ዋና መገለጫ እና ቅርፅ እንዲኖራቸው ይጠበቃል?

👉የሀገረ መንግሥት ሕልውን እና ቅቡልነትን የሚፈታተኑ ጉዳዮች፤

👉እንደ ሀገር በጋራ ስንኖር በየጊዜው አለመግባባቶችን እያስከተሉ ሀገራዊ አንድነታችንን የሚሸረሽሩ ጉዳዮች፤

👉በአፋጣኝ እልባትን የሚሹ ወቅታዊ ሀገራዊ ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ290 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ እየለማ መኾኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
Next articleከ47 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የከተማ መሬት ማስመለሱን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ገለጸ።