ከ290 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ እየለማ መኾኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

24

ባሕር ዳር: ጥር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የግብርና፣ አካባቢ ጥበቃ እና የውኃ ሃብት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የግብርና ቢሮን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው። የግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ ቃልኪዳን ሽፈራው ክልሉን በልማት ይቀይሩታል ተብለው ከታመነባቸው የልማት ዘርፎች አንዱ የመስኖ ልማት ነው ብለዋል።

በዘንድሮው የበጋ ወቅት አዳዲስ አሠራሮችን እና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከ290 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በመስኖ እየለማ ይገኛል።

በመስኖ እየለሙ ከሚገኙት የተለያዩ የሰብል ዓይነቶችም የተሻለ የምርት መጠን ይሠበሠባል ብለው እንደሚጠብቁም ነው የተናገሩት።

በበጀት ዓመቱ በአዲስ የመስኖ ልማት 43 ሺህ ሄክታር መሬት እየለማ ነው ያሉት አቶ ቃልኪዳን የግብርና አሠራርን በማዘመን እና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷልም ነው ያሉት።

የመስኖ ልማቱን ምርታማነት ከፍ ለማድረግም የአፈር ማዳበሪያ እና የውኃ መሳቢያ ሞተሮች ለአርሶ አደሮች እንደተሰራጨም አቶ ቃልኪዳን ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በጸጥታው ችግር ምክንያት ለጥቃት ተጋላጭ የኾኑ ሴቶችን ለመደገፍ እየተሠራ ነው” የምዕራብ ጎጃም ዞን
Next articleሀገራዊ አጀንዳ ምን አይነት ቅርጽ ሊኖረው ይችላል?