
ባሕር ዳር: ጥር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ያስገነባውን ዘመናዊ ስቱዲዮ እያስመረቀ ይገኛል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ መልዕክት አስተላልፈዋል።
“የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለአማራ ሕዝብ እና መንግሥት ማስተሳሰሪያ ገመድ ኾኖ እያገለገለ ያለ ተቋም” ስለመኾኑ ገልጸዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የክልሉን ሕዝብ እና መንግሥት ከማገልገል ባሻገር ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር በመቀናጀት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ስለመኾኑም ተናግረዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተደራሽነቱን ለማስፋት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የተቋሙን ጥረት ለመደገፍ በማሰብ ለሕንጻ ግንባታ የሚውል ቦታ ማስረከቡን አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በተረከበው ቦታ ላይ ተቋሙን የሚመጥን ሕንጻ በመገንባት ዓለማቀፋዊ ተቋም ለመኾን በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ድጋፉ እንደማይለይ አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!