
ባሕር ዳር: ጥር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) “የመፈፀም ዓመት” ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ሥራዎችን እያከናወነ ነው፡፡ በመፈፀም ዓመት ዕቅዱ ተደራሽ ለመኾን የሚያስችሉ የስቱዱዮ ግንባታ ማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ነው፡፡
አሚኮ ዋናውን መሥሪያ ቤት ጨምሮ አዲስ አበባ፣ ደሴ እና ጎንደር ያስገነባቸውን ዘመናዊ ስቱዱዮዎች እያስመረቀ ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና ለማኅበረሰብ ለውጥ የሚያግዙ መረጃዎችን እያደረሰ ነው፡፡
ዛሬም በሀገሪቷ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ መዲና በኾነችው አዲስ አበባ ያስገነባውን ዘመናዊ ስቱዱዮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ያስመርቃል፡፡
ከደቂቃዎች በኋላም የሚጀምረውን የአዲስ አበባ ስቱዲዮ የምረቃ ሥነ ሥርዓት በተለያዩ አማራጮች በቀጥታ ስርጭት ያደርሳል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!