የመቂ-ዝዋይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) እና ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ተመረቀ፡፡

397

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 26/2012 ዓ.ም (አብመድ) የመቂ-ዝዋይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር)፣ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳና የቀድሞ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም በተገኙበት ተመርቋል።

የመስኖ ፕሮጀክቱ ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው ነው፤ በመጠናቀቅ ላይ ያለው ሌላ የመስኖ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ደግሞ 15 ሺህ ሄክታር መሬት ማልማት እንደሚቻል ተገልጿል።

መሪዎቹ ከምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ቀደም ብለውም በዱግዳ ወረዳ የሚገኝን የችግኝ ጣቢያ መጎብኘታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

Previous articleከትናንት የምርመራ ውጤት ምን እንማር?
Next articleየጉምሩክ ኮሚሽን ባለፉት 9 ወራት 7 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ መያዙ አስታውቀዋል፡፡