
ባሕር ዳር: ጥር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ጥራቱን የጠበቀ የምጥና የወሊድ እንክብካቤ ለሁሉም እናት፤ ለጤናማ እናት” በሚል መሪ መልዕክት በዓለም አቀፍ ለ38ኛ፣ በሀገር አቀፍ ለ19ኛ ፣ በክልል ለ15ኛ ጊዜ የጤናም የእናትነት ወር የማጠቃለያ ሥነ ሥርዓት በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አበበ ተምትሜ የወሊድ እና የምጥ እንክብካቤን ጥራቱን በጠበቀ ማድረግ ይገባል ብለዋል። የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ እናቶች ከደም መፍሰስ፣ ከደም ግፊት እና ኢንፌክሽን ጋር በተያያዘ ለጤና ችግሮች እንዳይጋለጡ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት። ለውጤታማነቱ ደግሞ ዘርፈ ብዙ ርብርብ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
የሀገር ዋልታ የኾነችውን እናት ጤና ለማሻሻል ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት መሥራት አስፈላጊ ነው ያሉት አቶ አበበ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋት፣ ግብዓት እና በጀት በማሟላት የባለሙያዎችን አቅም ማጠናከር ውጤታማ ያደርጋል ብለዋል።
የድህረ ወሊድ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ እና ጥራቱን በማሻሻል እናቶች እና ሕጻናት ለአደጋ እንዳይጋለጡ ማድረግ ይቻላል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!