
ባሕር ዳር: ጥር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለቅዱስ መርቆርዮስ ዓመታዊ ክብረ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ የታሪክ አውድ ውስጥ ስሟ በደማቁ በሚጠራው ደብረ ታቦር ከተማ እና በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ መካነ ኢየሱስ በየዓመቱ በድምቀት ለሚከበረው የቅዱስ መርቆርዮስ ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
በፈረስ ጉግስ ትርዒት ታጅቦ የሚከበረው የቅዱስ መርቆርዮስ ክብረ በዓል ሃይማኖታዊ፣ ባሕላዊ እና ታሪካዊ ትውፊቱን ጠብቆ በማልማትና በማስፋፋት የልማት ጀግኖች መፍጠሪያ፣ ሁነኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ለማድረግ በቅንጅት መሥራት ይገባል ነው ያሉት።

በሀገር እና በዓለም አቀፍ የቱሪዝም መድረኮች ላይ የሕዝባችን የአደባባይ ልዩ ምልክት ሁኖ በጉልህ የሚነሳ አይነተኛ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲኾ በላቀ ትኩረት መሥራት የሁላችንም ኀላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው።
ርእሰ መሥተዳድሩ ለበዓሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
