
ባሕር ዳር: ጥር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሊባኖስ እና በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 456 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ እና ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ እንደቀጠለ ነው። በሳምንቱ 157 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
በዚህ ሳምንት ውስጥ ከሊባኖስ ወደ ሀገር የተመለሱት 157 ዜጎች መካከል 153 ሴቶች 4ቱ ደግሞ ጨቅላ ህፃናት ናቸው። ከተመላሾች መካከል 18 የሚኾኑት እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
በተያያዘ ዜና በሳምንቱ 289 ወንዶች፣ 9 ሴቶች 1 ጨቅላ ህፃናት በድምሩ 299 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ከተመላሾች መካከል ሦስቱ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ ታዳጊዎች መኾናቸው ታውቋል።
ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያ እና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራም እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከሴቶች እና ማኅበራዊ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሚያዚያ 04/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ሥራ እስካሁን 90 ሺህ 400 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!