ታጥቀው በጫካ የሚንቀሳቀሱ አካላት ወደ ሰላም በመመለስ የልማቱ አጋዥ እንዲኾኑ የተሀድሶ ሥልጣኞች ጠየቁ።

42

ጎንደር: ጥር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተሀድሶ ሥልጣኞች በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።

ለ10 ቀናት ሲሰጥ የነበረውን የተሀድሶ ሥልጠና በማጠናቀቅ ወደ ማኅበረሰቡ ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ የሚገኙት ሠልጣኞች የዓለም ቅርስ የኾነውን የጎንደር አብያተ መንግሥታት ዕድሳት፣ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን እና የመንገድ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ በጊዜያዊ የተሀድሶ ሥልጠና ማዕከል ሲሠለጥኑ የቆዩ ሠልጣኞች ከአሚኮ ጋር ባደረጉት ቆይታ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ገጽታ የቀየሩ ናቸው ብለዋል።

ከተሀድሶ ሥልጠናው አስፈላጊውን ትምህርት እና ግንዛቤ ያገኙ መኾኑንም ገልጸዋል። ሌሎች ታጥቀው በጫካ የሚንቀሳቀሱ አካላት ወደ ሰላም በመመለስ የልማቱ አጋዥ እንዲኾኑ ጠይቀዋል።

በአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ በጊዜያዊ የተሀድሶ ሥልጠና ማዕከል አሠልጣኝ እና አስተባባሪ በሪሁን እያሱ ለሠልጣኞች አስፈላጊው ሥልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸዋል።

ሠልጣኞቹ በከተማው እየተሠሩ ስላሉ የልማት ሥራዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማለም ጉብኝቱ መደረጉን አብራርተዋል።

ዘጋቢ፦ ዳንኤል ወርቄ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባኤ የድጋፍና የመልካም ምኞት መልዕክት ላከ።
Next articleበአማራ ክልል በሌማት ትሩፋት ትልቅ ለውጥ እየታየ መኾኑ ተገለጸ።