የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ይገኛል።

43

ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በትናንትናው እለት በደማቅ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የተጀመረው የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜው በጉባኤው አዘጋጅ አብይ ኮሚቴ ሪፖርት እና በሁለተኛው ጉባኤ የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

ጉባኤው በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ኮሚቴው በቀረበ ሪፖርት ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሪፖርቱን በውይይት አዳብሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በቀጣይ መርሀ ግብሩም በቀሪ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎች ያሳልፋል፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉበኤ ዛሬም በመካሄድ ላይ ነው።
Next articleየሰላም ጥሪን የተቀበሉ የታጠቁ አካላት ወደ ሕዝብ እና መንግሥት ተመለሱ።