
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ትናንት “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ ይውላል።
በጉባኤው የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህን የእንኳን መጣችሁ መልዕክት ተከትሎ የመክፈቻ ንግግሩን የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አድርገዋል።
የፓርቲው ፕሬዝዳንት በንግግራቸው የፓርቲውን የአምስት ዓመታት ስኬታማ ጉዞዎች የዳሰሱ ሲሆን፤ በቀጣይም ፓርቲው ሊያካናውናቸው ያሰባቸውን ጉዳዮች አመላክተዋል።
በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ የተጋበዙት የተለያዩ ሀገራት የእህት ፓርቲዎች ተወካዮችም በጉባኤው መክፈቻ ላይ መልዕክታቸውን እንዳስተላለፉም ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!