“ማኅበረሰቡ ፍፁም የሰላም አየር አስኪተነፍስ ድረስ ሕግ የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል” የምዕራብ ጎጃም ዞን

25

ፍኖተ ሰላም: ጥር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን የሥድስት ወራት የሕግ ማስከበር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው።

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት በምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፓለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ሙላት ጌታቸው በክልሉ ባጋጠመው የሰላም እጦት የክልል እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት በከፈሉት መሰዋዕትነት አንፃራዊ ሰላም መገኘቱን ተናግረዋል።

ባለው የሰላም እጦት ማኅበረሰቡ ለከፍተኛ ችግር መጋለጡን አንስተው ማኅበረሰቡ ፍፁም የሰላም አየር አስኪተነፍስ ድረስ ሕግ የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አቶ ሙላት የገለጹት።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ሙሉጌታ ዓለም የጸጥታ ችግሩን ለመፍታት የጸጥታ ኀይሉን ማጠናከር ወሳኝ በመኾኑ ባለፉት ሥድስት ወራት የሰላም አስከባሪ እና የሚኒሻ ኀይል በማደራጀት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ነው ያስገነዘቡት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የእህት ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎች ያስተላለፉት ዋና ዋና መልዕክት፦
Next articleየብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉበኤ ዛሬም በመካሄድ ላይ ነው።