
✍️ “ኢትዮጵያ ምንጊዜም የምስራቅ አፍሪካ ምሰሶ ነች”
የጅቡቲው ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ ኢልያስ ሙሳ ዳዋሌ
✍️ “የኢትዮጵያዊያን የአርበኝነት መንፈስ ለፀረ ቅኝ ግዛት እና አፓርታይድ ሥርዓት ትግል እንዲቀጣጠል አድርጓል”
የዚምባቡዌው ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ዋና ጸሐፊ ሲምበርሼ ሙቤንጌግዊ
✍️ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳቦች የኢትዮጵያን ብቻ ሳይኾን የአፍሪካን ብልፅግና ለማረጋገጥ ይበጃሉ”
የተርኪዬ ኤኬ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዛፈር ሲራካያ
✍️ “ጉባዔው ለኢትዮጵያ ቀጣይ እድገት አሻጋሪ እንደሚሆንና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ቦታ እንደሚያስቀጥል ባለሙሉ ተስፋ ነኝ”
የዩናይትድ ሩስያ ፓርቲ ሱፕሪም ካውንስል ቢሮ አባልና የሩስያ ፌዴሬሽን ሴናተር አንድሬ ክሊሞቭ
✍️ “በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳል የአመራርነት ጥበብ ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ትገኛለች”
የታንዛኒያው ቻማ ቻማ ፑንዱዚ ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ኢማኑኤል ቺምቢ
✍️ “ከሁለቱ አገራት ጠንካራ ግንኙነት ባለፈ በፓርቲ ለፓርቲ መካከል የትብብር ግንኙነቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል”
የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ዌላርስ ጋሳማጌራን
✍️ “ብልጽግና ፓርቲ ቃል የገባቸውን ተግባራት የፈጸመበት መንገድ እጅግ የሚደነቅ እና ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው”
የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ዋና ጸሀፊ ፒተር ላም
✍️ “የናይጀሪያና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመከባበርና በጋራ እሴት ላይ የጸና ነው”
የናይጄሪያው ኤፒሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀ-መንበር አልሀጅ አሊቡካር ዳሎሪ
✍️ “በአፍሪካ የአንድነት መሰረት እንዲጸና ልማትና ብልጽግና እንዲረጋገጥ በማድረግ ኢትዮጵያ የላቀ ሚናዋን እየተወጣች ነው”
የደቡብ አፍሪካው ናሽናል ኮንግረንስ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል ኑዶሎ ኪቤት