
ባሕር ዳር: ጥር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ትናንት የተጀመረው የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ ይውላል።
በጉባኤው የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን የእንኳን መጣችሁ መልዕክት ተከትሎ የመክፈቻ ንግግሩን የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አድርገዋል።
የፓርቲው ፕሬዚዳንት በንግግራቸው የፓርቲውን የአምስት ዓመታት ስኬታማ ጉዞዎች የዳሰሱ ሲኾን፤ በቀጣይም ፓርቲው ሊያካናውናቸው ያሰባቸውን ጉዳዮች አመላክተዋል።
በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ የተጋበዙት የተለያዩ ሀገራት የእህት ፓርቲዎች ተወካዮችም በጉባኤው መክፈቻ ላይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ ጉባኤው በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ሲካሄድ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
