“የኢትዮጵያ እና ኩባ ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው” አቶ አደም ፋራህ

38

ባሕር ዳር: ጥር 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ ልዑኳንን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የኢትዮጵያ እና ኩባ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

በአሁኑ ጊዜ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እና በሌሎች ዘርፎች ውጤታማ ስኬቶች እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፍጥነት እያደጉ ካሉ አምስት ሀገራት አንዷ መኾኗን ያነሱት አቶ አደም የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እያደገ መኾኑን ተናግረዋል።

ፓርቲው የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማሳካት በአምስት ዘርፎች በልዩ ትኩረት እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል። በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱንም አንስተዋል። በጤና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የተሻለ ሥራ ለማከናወን ትብብር እንደሚጠናከር የገለጹት አቶ አደም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትና የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሠራል ብለዋል።

የኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል እና የልዑካን ቡድኑ ዩዲ ሜርሴዲስ ኸርናንዴዝ የሁለቱን ሀገራት ለዘመናት የዘለቀ ቤተሰባዊነት የተላበሱ ግንኙነቶችን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል። በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ፓርቲያቸው እንዲሳተፍ በመጋበዙ ትልቅ ምስጋና አቅርበዋል።
ውይይቱ ሀገራቱ በኢንቨስቶመንት፣ በዲፕሎማሲ እና በሌሎች መስኮች ግንኙነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ነው ብለዋል።

ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት በማጠናከር የሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ያላቸውን የጋራ ታሪክ የሚያጠናክር፣ ዕድገታቸውንም የሚያጎለብቱ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአምባሳደሮች ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ በታማኝነት የማገልገል ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አሳሰቡ።
Next articleየብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።