አምባሳደሮች ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ በታማኝነት የማገልገል ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አሳሰቡ።

32

አዲስ አበባ: ጥር 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኾነው የተሾሙት አዲሱ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም ቃለመሐላ ፈጽመው ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ መመሪያ ተቀብለዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አምባሳደሮች ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ በታማኝነት የማገልገል ኀላፊነት አለባቸው ብለዋል። በተለይም አዲሱ ተሿሚ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በጥበብ እና በብልሀት የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት እንዲያስቀጥሉ አደራ ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ለ120 ዓመታት የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መኾናቸውን ገልጸዋል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በዜጋ ዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በጸጥታ እና ደኅንነት የኢትዮጵያን ጥቅም በማስጠበቅ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት የማጠናከር ኀላፊነት አለባቸው ብለዋል።

ለአዲሱ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርም የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም ባለፈው ኅዳር/2017 ዓ.ም በፕሬዚዳንቱ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ኾነው መሾማቸው ይታወሳል።

ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ1 ሺህ 400 ሊትር በላይ ቤንዚን ተያዘ።
Next article“የኢትዮጵያ እና ኩባ ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው” አቶ አደም ፋራህ