
ገንዳውኃ: ጥር 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን በገንዳውኃ ከተማ አሥተዳደር በሕገ ወጥ መንገድ ተዘዋውሮ ሊሸጥ ተብሎ የተቀመጠ ከ1 ሺህ 400 ሊትር በላይ ቤንዚን በተደረገ በማኅበረሰቡ ትብብር እና በጸጥታ ኃይሉ ፍተሻ መያዙን የገንዳውኃ ከተማ አሥተዳደር ንግድ እና ገቢያ ልማት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የገንዳውኃ ከተማ አሥተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ ወይዘሮ ሙሉዬ አየልኝ እንደገለጹት ማኅበረሰቡ ባደረገው ትብብር እና የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው ፍተሻ ተይዟል ነው ያሉት።
በከተማ አሥተዳደሩ ተዘዋውሮ በጥቁር ገበያ ሊሸጥ ተብሎ በዝግጅት ላይ እንደነበርም ኀላፊዋ ተናግረዋል።
ምክትል ኀላፊዋ አክለውም ማኅበረሰቡ ላደረገው ትብብር አመስግነው ቀጣይም እንዲህ ዓይነት ወንጀል ሲያጋጥም ጥቆማ እንዲሠጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
