
ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን 85ኛውን የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ምስረታ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሚኒስትሯ “የአገው ፈረሰኞች በዓል ፌስቲቫል ታሪካችንን፣ አብሮነታችንን፣ ባሕላችንን አስተሳስሮ በማቆየት ለዘመናት የኖረ የማኅበረሰባችን እሴት ነው” ብለዋል።
እሴቱን መጠበቅ እና ማልማት እንደሚያስፈልግ ገልጸው በዓሉን ባሕላዊ እሴቶቻችንን በማዳበር፣ በመጠበቅና አብሮነታችንን ለዓለም በማሳየት ልናከበር ይገባል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
