ከተማ ውስጥ የነበሩ የጽንፈኛ ኀይል አባላት በቁጥጥር ውለዋል።

64

ባሕር ዳር: ጥር 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ጎጃም ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ የስድስት ወር የተግባር አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። የሰሜን ጎጃም ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ገብረሥላሴ ታዘብ በዞኑ ከ500 በላይ የመሸገ የጸረ ሰላም ኀይል አባላት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተናግረዋል።

መምሪያ ኀላፊው ኀብረተሰቡ በጽንፈኛ ኀይሉ እኩይ ምግባር በመማረሩ ከመንግሥት ጥምር የጸጥታ ኀይሉ ጋር ተናቦ እየሠራ ነው ብለዋል።

ከሕዝብ ጋር በተሠራው ሥራም በከተማ ውስጥ የመሸገ የመረጃ እና የሎጀስቲክስ የጽንፈኛው ኀይል አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል ነው ያሉት።

ጽንፈኛው ኀይል ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል ያሉት መምሪያ ኀላፊው በአሁኑ ወቅት በጠላት እጅ የወደቀ ከተማ እንደሌለም አስረድተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአገው ፈረሰኞች በዓል ለፌስቲቫል ቱሪዝም ገቢ ተቋዳሽ ለመሆን ያመቻቻል” ቢልለኔ ስዩም
Next articleየአገው ፈረሰኞች በዓል የባሕል እሴቶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ ጉልህ ሚና እየተወጣ ነው።