ሱዳን ባለፉት 24 ሰዓታት 59 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በምርመራ አረጋገጠች፡፡

139

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 25/2012 ዓ.ም (አብመድ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 59 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን እና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ወደ 592 ማሻቀቡን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት አምስት ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን ማጣታቸውንና የሟቾቹ ቁጥር ወደ 41 ከፍ ማለቱ በሪፖርቱ አሳይቷል፡፡ ስድስት ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገሙ ሰዎች ቁጥር በሱዳን 52 ደርሷል፡፡

በሀገሪቱ ካሉ 18 ግዛቶች በ14ቱ ቫይረሱ መከሰቱን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አረጋግጧል፡፡ በቫይረሱ ከፉኛ በተጎዳችው ርእሰ መዲናዋ ካርቱም ቫይረሱን ለመቆጣጠር ፖሊስ ርምጃ እየወሰደም ነው ተብሏል፡፡

በከተማዋ በሚገኙ 200 መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ 1ሺህ 365 ተጨማሪ የፖሊስ አባላትን ማሰማራቱንም የሀገሪቱ ፖሊስ ቃል አቀባይ ዑመር አብዲል ማጂድ ተናግረዋል፡፡

በሱዳን የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ካለፈው ሚያዚያ 10/2012ዓ.ም ጀምሮ የእንቅስቃሴ እገዳ መጣሉ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን
በታዘብ አራጋው

Previous articleከዛሬው የምርመራ ውጤት ምን እንማር?
Next articleበደብረ ታቦርና ወረታ ከተሞች በሦስት ቀናት ብቻ 671 ዩኒት ደም ተሰብስቧል፡፡