
ባሕር ዳር : ጥር 23/2017 ዓ.ም(አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተመስገን ጥሩነህ ለአገው ፈረሰኞች በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ምክት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአገው ፈረሰኞች የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እና ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ታላቅ ሚና ነበራቸው። ለዚህም የዓድዋ ዘመቻ ተሳትፏቸው ጉልሕ ምስክር ነው” ብለዋል።
ዛሬም የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል ሰላምንና ጸጥታን በማስከበር ተገቢውን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ዛሬ የሚከበረው በዓል፣ ፈረሰኞቻችንና ፈረሶቻችን የሰላምና የልማት ዘብ መሆናቸውን ለትውልድ የሚመሰክሩበት እንደሚሆን አምናለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።
በዓሉ መልካም በዓል እንዲኾንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!