
ባሕር ዳር : ጥር 23/2017 ዓ.ም(አሚኮ) በኮንትሮባንድ እና በሕግ ሽፋን አማካኝነት ወደ ሀገር የሚገቡ የብረታ ብረት ምርቶችን ለመቆጣጠር እየተሠራ መኾኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ በኮንትሮባንድ እና ሕግ ሽፋን ባደረገ መልኩ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች፤ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅማቸውን የሚቀንሱ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል።
ግብረ ኀይል በማቋቋም በክልል እና በከተማ ያለውን የኮንትሮባንድ ንግድ የመቆጣጠር ሥራ እየተሠራ መኾኑን አስታውቀዋል።
የብረታ ብረት ኢንዱስትሪውን ጨምሮ አጠቃላይ የሀገሪቷን ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ የኾኑ ኢንዱስትሪዎችን ከኮንትሮባንድ እና ከሕገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመከላከል በትኩረት እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።
ሕገወጥነትን መከላከል የመንግሥት ኀላፊነት ብቻ አለመኾኑንም ገልጸዋል። ኅብረተሰቡ ማንኛውንም ሕገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በማጋለጥ የዜግነት ኀላፊነት መወጣት አለበት ነው ያሉት።
ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ጠንቅ የኾነውን የኮንትሮባንድና ሕገ ወጥ ንግድ ለመከላከል በሚሠራው ሥራ ማኅበረሰቡ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!