“ፈረሱም ያው፣ ሜዳውም ያው”

43

እንጅባራ: ጥር 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ ፈረስ እና ሜዳ ተገናኝተው ለተመልካች አይን እንግዳ ነገር የሚያሳዩበት ቀን ነው። በአገው ምድር በ85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ላይ ነን።

በዓሉ በየዓመቱ ጥር 23 በእንጅባራ ከተማ በድምቀት ቢከበርም የዘንድሮው ድምቀት ግን ላቅ ያለ ስለመኾኑ የተደረገው ዝግጅት ይነግራል።

የክልል እና የፌዴራል መንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ይታደሙበታል። የሀገር ውስጥ እና የውጭ እንግዶችም ገብተዋል። እንጅባራ እንግዶቿን ከዋዜማውም ቀድማ ተቀብላ ስታስተናግድ ሰንብታለች። ዛሬ ደግሞ ፈረሰኞች ፈረሶቻቸውን ሸልመው ከትመዋል። ለእንግዶች ልዩ ነገር አሳይተው ልዩ ሀሴትን ያደርጋሉ።

ፈረሱም ያው፣ ሜዳውም ያው ነው። ከቆይታ በኃላ ሁሉም አይነት የፈረስ ትርኢት ይጀምራል።

የአካባቢው ጸጋ እና መለያ የሆኑ ባሕላዊ ምግቦች እና መጠጦች፣ ባሕላዊ አልባሳት እና መገልገያ እቃዎች እንዲሁም አካባቢው የሚያበቅላቸው አዝዕርት በሙሉ ለዕይታ ቀርበዋል።

ይህን ሁሉ ትዕይንት ባሉበት ኾነው ለመከታተል ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁሉም አይነት የማሰራጫ አማራጮች ጋር ይወዳጁ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አዲስ አበባ ገቡ።
Next article“የአገው ፈረሰኞች በዓል ባሕላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበርና እንዲለማ የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊነቱን ይወጣል” አቶ መልካሙ ፀጋዬ