
ባሕር ዳር : ጥር 23/2017 ዓ.ም(አሚኮ) የብሪክስ አባል ሀገር እህት ፓርቲ የሩሲያው ዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዲ .ኤ ሜዴቭዴቭ በብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ምክትል ሊቀመንበሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ (ዶ.ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከዛሬ ጥር 23 እስከ 25 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል”በሚል መሪ መልዕክት ይካሄዳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!