አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ ለአገው ፈረሰኞች በአል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት !

40

ፈረስና ፈረሰኛ በልሂቃን ዘንድ የክብርና የጀግንነት ምልክቶች ናቸው።

አገዎች የበዛ ባሕል፣ ተዝቆ የማያል ትውፊት፣ ውድ ማንነት፣ ቅይጥ እሴት ያላቸው የመቻቻልና የአብሮነት ማሳያዎች ናቸው።

በኢትዮጵያ አንድነት አገዎች የዘመንታሪክ ካስማ እና ማገር ከሆኑ ሕዝቦች መካከል ባለታላቅ አሻራ ባለቤቶች ናቸው።

እንኳን ሰዎቹ ፈረሶቻቸውም በሀገረ መንግስት ምስረታ ዘመን የማይሽረው ገድል የፈፀሙ የክብርና የጀግንነት ምልክቶች ናቸው።

አገዎች ፍቅር የተካኑ፣ ለሰላም ዋጋ የሚሰጡ፣ ግጭት የማያናውጣቸው ፣ የብዝኃነት ጌጥ፣ የአንድነት ማሳያ፣ የሰውነት ልክ ሚዛን በልካቸው ያጌጡ፣ ሕዝቦች ናቸው ።

የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ለሀገራቸው የከፈሉት ዋጋ ና የፈረሶቻቸውን ገድል ያለማቋረጥ በማሰብ ውለታ አክባሪነቱን በተግባር ያሳየ የአገውን ሕዝብ ባሕልና እሴት በትውልድ ቅብብሎች ለዚህ ከፍታ ያበቃ ዘመናዊ የአመራር ስርአት ምሳሌ ማኅበር ነው።

አገዎች የዛሬዋ ኢትዮጵያ አሁንያለችበት ከፍታ እንድትደርስ የከፈሉት ዋጋ ትልቅ ነው። ነገ የምናስባት ኢትዮጵያ ለመገንባትም ከሌሎች ወንድምና እህት ሕዝቦች ጋር በጋራ የምንመኛት የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በሚደረገው ሁሉንአቀፍ ጥረት የአገው ሕዝብ ሚና ከፍተኛ ነው።

በተለይም በክልላችን አስተማማኝ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የምታደርጉትን ጥረት አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እያሳሰብኩ።

እንኳን 85ኛው የአገው ፈረሰኞች ቀን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

መልካም በአል!!

Previous articleየብልጽግና ፓርቲ አማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ለአገው ፈረሰኞች በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት!
Next articleየዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አዲስ አበባ ገቡ።