የብልጽግና ፓርቲ አማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ለአገው ፈረሰኞች በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት!

28

እንኳን ለ85ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ዓመታዊ ክበረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

እንኩዋ 85ንቲ አገው ፌሬስቴንካው ጌርክስ ዴክስ ታምፁናስ!

የአገው ሕዝብ ቱባ ባሕላዊ እሴት መገለጫ፣ ሌላኛው የቱሪዝም መዳረሻ እና ግሩም የሀገር ሀብት የሆነው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር፤ አንድም የቅድስና እና የነፃነት ምልክት በሌላ በኩልም ስፓርትና የማሕበራዊ ሁነቶች መከወኛ የሆነውን ፈረስ ያላቸውንም ሆነ የሌላቸውን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን በአባላት አቅፎ የያዘ መሰረተ ሰፊ እና ዘመን ተሻጋሪ ማኅበራዊ ተቋም ነው፡፡

ማኅበሩ የአካባቢው ማኅበረሰብ የእርስ በርስ መገናኛ፣ የናፍቆት መወጫ እና የአንድነት ሰበዝ ሁኖ የሚያገለግል የተዋበ እና የደመቀ ባሕላዊ መድረክ ነው፡፡ የአገው ፈረሰኞች ማኅበር በልማት እና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የአዊ ብሔረሰብ ዞን የትናንት ወረት፣ የዛሬ ጥረት እና የነገ ትልም ላይ የላቀ መግባባትን ለመፍጠር የሚያግዝ ሁነኛ መሳሪያ ሁኖ ያገለግላል፡፡

ጠንካራ አደረጃጃት ያለው፣ የሕዝብ የአደባባይ አንደበት፣ የአዊ ብሔረሰብን እምቅ የባሕል እና የቱሪዝም ሀብት የሚገልጥ፣ ኢኮኖሚውን የሚደጉም፣ ገበያንም ይበልጥ የሚያነቃቃ፣ ይበልጡንም ለሀገር ፍቅርና ለብሔራዊነት መግባባት የሚጫወተው ሚና የላቀ ነው፡፡

ንቅናቄን በሚሹ አካባቢያዊ፣ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እና መግባባትን እና የአስተሳሰብ ለውጥን በሚሹ ጉዳዮች ላይ ሁሉ መንግስትንና ሕዝብን ለማገናኘት እና በትብብር ለመሥራት የሚጫወተው ሚና እጅግ የላቀ ነው፡፡

በመሆኑም የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ባሕልና ልማትን አቀናጅቶ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና ለውጥ ለማምጣት ያለውን አውንታዊ ሚና አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡

በድጋሜ እንኳን ለ85ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ዓመታዊ ክበረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለ85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት!
Next articleአፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ ለአገው ፈረሰኞች በአል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት !