
እንኳን 85ኛው ለአገው ፈረሰኞች ቀን አደረሳችሁ! እንኳን ታምፁናስ! ከዛሬ 85 ዓመት በፊት ለተመሰረተውና በሕዝባዊ መሰረቱ ፀንቶ ለቆየው ለአገው ፈረሰኞች በዓል እንኳን አደረሳችሁ። የአገው ሕዝብ የሀገሩን ክብር፣ አንድነት እና ማኅበረሰባዊ ማንነቱን በሁለተናዊ ጀግንነቱ አፅንቶ የኖረ ሕዝብ ነው፡፡
ይህ ቀደምት እና ሥልጡን ሕዝብ ታሪኩን፤ባህሉን እና እሴቱን ጠብቆ ያቆየበት ትጋትና በሌሎች ኢትዮጵያውያንም ዘንድ እንዲከበሩ ለማድረግ ያሳየው ሥልጡን አካሄድ የሕዝቡን ጥንታዊነት፤የቱባ ባሕሎች ባለቤትነት ብቻ ሳይሆን በዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ፈር ቀዳጅ ሕዝብ መሆኑን በልበ ሙሉነት መናገር ይቻላል፡፡
የዚህ ኩሩ ሕዝብ ፍሬ የሆነው የአገው ፈረሰኞች ማኅበርም ቀደምት አባቶቻችን ለኢትዮጵያ ልዑዋላዊነትና አንድነት በጀግንነት የከፈሉትን ሰማዕትነት በክብር እየዘከረ ከሦስት ትውልድ በላይ ተሻግሯል፡፡ይህም የአገው ሕዝብ ሀገሩን እና ለሀገሩ ክብር ዋጋ የከፈሉትን ሁሉ አክብሮ የሚያስከብር አመስጋኝ ሕዝብ መሆኑን ያሳያል፡፡
ዘንድሮም የሀገር ባለውለታ የሆኑ ጀግና ፈረሰኞች ከነ ሥልጡን ፈረሶቻቸው በሚዘከሩበት የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከፍ ብለው ይታዩበታል፡፡
የአገው ፈረሰኞች እና ሌሎች ቀደምት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጋር ተባብረው ነጻነታችንን ማስከበር እንደቻሉት ሁሉ ፤ እኛም የዚህ ዘመን ትዉልድ አባላት ትናንት እነዚያ አባቶቻችን የነበራቸዉን የሰንደቅዓላማ ክብር እና ለሀገር የከፈሉትን መስዋዕትነት በማስታወስ ወቅቱ የሚጠይቀዉን የብሔራዊ አርበኝነት ግዳጅ ልንወጣ ይገባል፡፡
በዓሉ በዓመታት ሂደት ዉስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ባሕላዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ ሁሉ ልባዊ ምሥጋናዬን እያቀረብኩ ፣ የአገው ፈረሰኞች በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብም የተጀመሩት ተግባራቶች እንዲሳኩ የክልሉ መንግስት አስፈላጊዉን ሁሉ እያደረገ እና በቀጣይም የሚያደርግ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ ፡፡ አመሰግናለሁ!!
መልካም በዓል!
እንኩዋ 85ንቲ አገው ፌሬስቴንካው ጌርክስ ዴክስ ታምፁናስ!
አዊው እዝብ አጌሩሳ ክብሮስታ እምፕልቶ ጚው አይትሊ እምትጝፃማ እጅፅኹ እዝብያኽ፡፡
እን እዝብ ጚውሳ ባይሎ ማንዳማ እጅፅጝ እሊኩ ይቶፒያው እዝብካስ ካንትፂያኽ፡፡
አዊው እዝብ እን ጊሪምፂ ባይል ዌና ይኹቺ ያኻውላ ዲሞክራሲያዋ ያኹኽ ታክስጚስ ቤራዊ እምፕልቶ ካንፅፅኹ እዝብ አኽጝ ኪላ ማሊስቴ፡፡
እን እዝቡ ዋይሚ ያኹኽ አገው ፌሬስቴንካው ማቢሪ ኪላ ቤዴራስኩ ታብል ይቶፒያው እምፕልትስ ኬዩኑሳ ጄግንቶ ክብርስ ዜኬራማጊ ሹኻ ክምንትዴስ ጃላ ካይጝፃ፡፡
እን ያኽጝስ ኪላ አገው ፌሬስቴንካው ባልዳ ዋሺኒዴስኪ ጊዝዴስ ጃላ ይቶፒያ ስታ ይቶፒያውት ኬፍ ንካማ ካንትስታኑዊያኽ፡፡
ካብስ እንኩዋ 85ንቲ አገው ፌሬስቴንካው ጌርክ ባልስ ዴክስ ታምፁናስ ባል ሰላሙ እንካንጚውስታ ኬቤቤርጚው ያኻታ እንጉስቴ!