
እንጅባራ: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ85ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ዋዜማ ደምቋል።ከድምቀቶቹ መካከል “ሚስ አገው” ወይም የአገው ቆንጆ የቁንጅና ውድድር ይገኝበታል። ይህ የቁንጅና ውድድር ለቀጣይ አንድ ዓመት ያህል የብሔረሰቡ የባሕል አምባሳደር በመኾን የምታገለግለዋ ቆንጆ ሴት ትታወቅበታለች።
በመርሐ ግብሩ ላይ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ፣ የክልል እና የፌዴራል መንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ይታደማሉ።
የቁንጅና ውድድሩን የአሚኮ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ምንችል እንግዳ፣ ተዋናይት መስከረም ነጋ እና ተዋናይ እና ደራሲ ደሳለኝ መኩሪያ በዳኝነት ሊመሩት ተሰይመዋል። ከደቂቃዎች በኋላ ሚስ አገው ትለያለች።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!