የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ ፒተር ላም ቦዝ በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ።

36

ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ ፒተር ላም ቦዝ በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብቷል።

ዋና ጸሐፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአገው ፈረሰኞች በዓል ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ከሚመለከታቸው ጋር ሁሉ የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን”
Next article“እየተከናወኑ ያሉ መሠረተ ልማቶች የነዋሪዎችን ፍላጎት የሚመጥኑ ናቸው” ኢንጅነር አይሻ መሐመድ